በከተማዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተመልክተናል:- የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች

You are currently viewing በከተማዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተመልክተናል:- የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተመልክተናል ሲሉ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ የሚደካሄደውን የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁና በመገንባት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከጎበኟቸው የልማት ስራዎች መካከልም የለሚ እንጀራ ማዕከል ፣ የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቪሽንና ኮንቬሽን ማዕከል እና የለሚ ኩራ የገበያ ማዕከል ይገኙበታል።

የልማት ስራዎቹ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የኑሮ ውድነትን የሚያረጋጉ እና የከተማዋንም ገጽታ ከፍ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።

እነዚሁ የልማት ስራዎች ፓርቲው ቃል የገባቸውን በተግባር ያረጋገጠበት ማሳያ ነው ብለዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review