AMN ጥር 9/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በከተራ እና በጥምቀት በዓላት አከባበር ወቅት በከፍተኛ ወጪ በከተማዋ የለሙ አረንጓዴ ቦታዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አብያተክርስቲያናት፣ ካህናት እና በዓሉን የሚያስተባብሩ ወጣቶች በዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ለምዕመኑ መልእክት እንድታስተላልፉ ጠይቀዋል።
ቢሮው በአረንጓዴ ስፍራዎች ላይ ለጥንቃቄ የሚረዱ ምልክቶችን እንደሚያደርግ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም አስታውቋል።
የመገናኛ ብዙኃን ህብረተሰቡ ለአረንጓዴ ቦታዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ሥራ እንዲሰሰሩም ቢሮ ሀላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል።
በአሰግድ ኪዳነ ማርያም
All reactions:
8383