በክሮሺያ በተደረገ የአትሌቲክስ ውድድር ጉዳፍ ፀጋዬ አሸነፈች

You are currently viewing በክሮሺያ በተደረገ የአትሌቲክስ ውድድር ጉዳፍ ፀጋዬ አሸነፈች

AMN-ግንቦት 16/2017 ዓ.ም

በክሮሺያ ዛግሬብ በተደረገው ኮንቲኔንታል ቱር አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጥሩ ውጤት አምጥተዋል።

በሴቶች 1500 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር አሸንፋለች።

ጉዳፍ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 3:58.14 የሆነ ሰዓት ወስዶባታል ።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ብርቄ ኃየሎም በ3:59.19 ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ሳምራዊት ሙሉጌታ ደግሞ ስድስተኛ መውጣት ችላለች።

በሌላ ውድድር በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ቢኒያም መሀሪ በ13:03.57 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review