በኮሪደር ልማት የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሰፊ የጥበቃ ስራ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባልስልጣን አስታወቀ

You are currently viewing በኮሪደር ልማት የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሰፊ የጥበቃ ስራ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባልስልጣን አስታወቀ

AMN – የካቲት 4/2017 ዓ.ም

ባለስልጣኑ የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸሙን የገመገመ ሲሆን በቀጣይ በሚሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያም ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር መክሯል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት 6 ወራት የደምብ ጥሰቶችን እና መተላለፎችን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑ ተገልጿል።

በኮሪደር ልማት የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ማድረግ እና ግንባታው ሳይስተጓጎል እንዲካሄድም በግማሽ ዓመቱ ሰፊ ስራ መከናወኑን የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ ተናግረዋል።

ከዚያ ባለፈ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ንብረት ያለ ችግር እንዲጓጓዝና እንዲጠበቅ መደረጉንም ተናግረዋል።

የደንብ ጥሰቶች ሳይፈፀሙ አስቀድሞ ለመከላከል የግንዛቤ ስራ በት/ቤቶች፣ በአደባባዮች እና በተለያዩ አካበቢዎች መሰራቱንም የባለስልጣኑ ስራ አሰኪያጅ ተናግረዋል።

የንግድ ስርዓቱ ጤናማ እንዲሆን እና ደንብ የሚተላለፉ ነጋዴዎች ላይም በግማሽ ዓመቱ ርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፉ ግለሰቦችን እና ተቋማት ላይ በወሰደው ርምጃም ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉም ተገልጿል።

በግማሽ ዓመቱ የስነ ምግባር ጉድለት በታየባቸው የደንብ ማስከበር አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱም ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በበጎ ተግባር ላይ ተሳትፎ ስለማድረጉም በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

በአሰግድ ኪዳነ ማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review