በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን እኩለ ሌሊት ወደ ቻይና አቀና

You are currently viewing በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን እኩለ ሌሊት ወደ ቻይና አቀና

AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን እኩለ ሌሊት ወደ ቻይና ናንጂንግ አቅንቷል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሀመድን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በሽኝት መርሀ-ግብሩ ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አትሌት የማነ ፀጋይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ልዑክ ቡድኑን በማበረታታት ሽኝት አድርገውላቸዋል።

ልዑክ ቡድኑ 12 አትሌቶች ፣ 2 አሰልጣኞች፣ አንድ ቡድን መሪ ፣ አንድ ቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ እና አንድ ፊዝዮቴራፒስት ያካተተ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review