በየመን ባህር ዳርቻ በጀልባ መስመጥ አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አለፈ

You are currently viewing በየመን ባህር ዳርቻ በጀልባ መስመጥ አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አለፈ

AMN – ጥር 14/2017 ዓ.ም

ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት ላይ 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመናዊ ካፒቴን እና ረዳት ካፒቴን ጋር የያዘች ጀልባ ከጂቡቲ ተነስታ በባኒ አል-ሃካም ከተማ አል-ሃጃጃህ አቅራቢያ መስጠሟን በየመን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

በአደጋው የዘጠኝ ሴቶች እና የአስራ አንድ ወንዶች ህይወት በድምሩ የ20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ህይወት አልፏል።

ከአደጋው የቀሩት 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን የበረራ ሰራተኞች መትረፍ ችለዋል።

ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም፣ እ.ኤ.አ. በ2024 ብቻ ከ60,000 በላይ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች የመን መድረሳቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን በየጊዜው ከጂቡቲ ወደ አገር ቤት የመመለስ ስራ እየሰራ ቢሆንም በህገ-ወጥ ስደት ምክንያት የበርካታ ዜጎች አካል ከመጉደሉም በላይ የብዙዎች ህይወት እያለፈ ይገኛል ተብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ እና የሚመለከተው መንግስታዊ አካል ይህን ህገ-ወጥ ተግባር ለመከላከል እና የዜጎችን ህይወት ለመታደግ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ መልእክት መተላለፉን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review