AMN-የካቲት 17/2017 ዓ.ም
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል ግቢ ውስጥ ውሀ በአቆረ ጉድጓድ ውስጥ ዋና ለመዋኘት የገቡ ሶስት ታዳጊዎች ህይወት አልፏል።
ታዳጊዎቹ ትላንት እሁድ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ኳስ ሲጫወቱ ቆይተው በዕጽዋት ማዕከሉ ጊቢ ውስጥ ባለው ውሀ በአቆረ ጉድጓድ ውስጥ ዋና ለመዋኘት ገብተው ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ተናግረዋል።
የኮሚሽን መ/ቤቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊዎቹን አስከሬን አውጥተው ለፖሊስ አስረክበዋል።
የታደጊዎቹ ዕድሜ ሁለቱ የ13 ዓመት ሲሆኑ አንደኛዉ ደግሞ 16 ዓመቱ መሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች በተቆፎረው ውሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ውስጥ ዋና ለመዋኘትና ለመታጠብ በሚል በተለይ ታዳጊዎችና ወጣቶች እየገቡ ህይወታቸውን ያጣሉ ።
ስለሆነም ጉድጓዱን የቆፈሩና በዉሀ የሚጠቀሙ አካላት ተገቢዉን የአደጋ መከላከል ስራ የማከናወን ኃላፊነት ያለባቸዉ በመሆኑ እያጋጠመ ያለዉን አደጋ አሰቀድሞ በመከላከል በኩል ግዴታቸዉን እንዲወጡ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
ወላጆችና የአካባቢዉ ማህበረሰብም ለታዳጊዋች አስፈላጊዉን ጥበቃ እንዲያደርጉም ኮሚሽን ጠይቋል።