ባህርዳር የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን ወደከፍታ በሚወስድ ሥራ ላይ ትገኛለች- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ባህርዳር የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን ወደከፍታ በሚወስድ ሥራ ላይ ትገኛለች- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ ባህርዳርን ወደ ስማርት ሲቲ ለማሸጋገር ከሚረዱ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት በፍጥነት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መመልከታቸውን አንስተዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የጣና ሐይቅ እና የዓባይ ወንዝ መናገሻ የሆነችውን ባህርዳርን ይበልጥ የውበት ግርማ የሚያላብሱ እንዲሁም የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን ከፍ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።

ከምንም በላይ በኮሪደር ልማት እየዋሉ ያሉ አስፈላጊ ግብዓቶች በአብዛኛው በክልሉ የሚመረቱ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ እንደሆነም አመላክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review