ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ከ5.7 ሚሊየን ብር በላይ መቅጣቱን ገለጸ

You are currently viewing ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ከ5.7 ሚሊየን ብር በላይ መቅጣቱን ገለጸ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በዛሬው እለት 5 ሚሊየን 775 ሺህ ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1 ሚሊየን 595 ሺህ ብር፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 1ሚሊየን150 ሺህ ብር፣ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 1 ሚሊየን 50 ሺህ ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 650 ሺህ ብር፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 640 ሺህ ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

በተያያዘም በቦሌ ክፍለ ከተማ 300 ሺህ ብር፣ በአቃቂ ክፍለ ከተማ 300 ሺህ ብር፣ በልደታ ክፍለ ከተማ 70 ሺህ ብር፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 20 ሺህ ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 27 ጅርጅቶች እና 15 ግለሰቦች በመቅጣት በድምሩ 5 ሚሊየን 775 ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review