ባለፉት 6 ወራት በቀን 25 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሀ አቅርቦት ተጨምሯል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት በቀን 25 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሀ አቅርቦት ተጨምሯል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 12/2017 ዓ.ም

በ2017 በጀት አመት ያለፉት 6 ወራት 15 የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ በቀን 25 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሀ አቅርቦት መጨመር መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓም ያለፉት 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ሥራዎችን በተመለከተ ነባር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት እየተከናወነ መሆኑን ያወሱት ከንቲባ አዳነች አሁን ካው አቅርቦተወ በተጨማሪ የ15 ተጨማሪ ጉድጓዶች ቁፋሮ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በተጨማሪ በቀን 100 ሺ ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው በኦሮሚያ ቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኘው የጩቋላ ከርሠ ምድር የውሀ ልማት ፕሮጃክት 13 ጉድጓድ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በቀን 80 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሀ መገኘቱን አስረድተዋል። 7 ተጨማሪ ጉድጓድ በቁፋሮ ላይ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡

በቀን 73 ሺ ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው የገርቢ የውሃ ግድብ ፕሮጀክትን ለመገንባት ተወስኖ በሂደት ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

መሰረታዊ የመጠጥ ውሃ የአቅርቦት ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ የከርሠ ምድር ውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ጥናት በአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት እየተጠና እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

የፍሣሽ ሥራዎችን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በቀን 30 ሺ ሜትር ኪዩብ (3ዐ ሚሊዬን ሊትር) ማጣራት የሚችል የቦሌ አራብሳ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ መጠናቀቁን አስታውሰዋል፡፡

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review