AMN- የካቲት 19/2017 ዓ.ም
ባለፉት ሰባት ወራት ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ ገለጹ።
ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ፤ ለገቢው መገኘት ወርቅ፣ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ኤሌክትሪክ እና የቁም እንስሳት ኤክስፖርት ለውጤቱ መገኘት ከፍቸኛ አስተዋጽኦ በማበርከት የእቅዳቸውን ከ100% በላይ አፈጻጸም ማስገኘት የቻሉ የወጪ ንግድ ምርቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሰባት ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው የ1.9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ1.94 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ101.2% ብልጫ እንዳለዉ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
አፈፃፀሙ ይበልጥ እንዲጠናከር ጥብቅ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረጉ የተናገሩት ሚኒስትሩ የወጪ ንግድ ዘርፍ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት ያለሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።