ባለፉት ስድስት ወራት በኮሪደር ልማት ስራ የተሻለ የሰው ሀይልን በማፍራትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል፡- አቶ ጥራቱ በየነ

You are currently viewing ባለፉት ስድስት ወራት በኮሪደር ልማት ስራ የተሻለ የሰው ሀይልን በማፍራትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል፡- አቶ ጥራቱ በየነ

AMN – ጥር 14/2017 ዓ.ም

ባለፉት ስድስት ወራት በኮሪደር ልማት ስራ የተሻለ የሰው ሀይልን በማፍራትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

ቢሮው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የአቅም ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

በመረሀ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የኮሌጆች የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ግምገማው ያለፍትን ጥሩ ተሞክሮዎችን በማጠናከር እና ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ ስራዎች የቤት ስራ የሚሰጥ ነው ያሉት አቶ ጥራቱ በየነ በተለይ በተቋማት አቅም ግንባታ ላይ በተሰራው ስራ ለውጥ ማምጣት ስለመቻሉ አመልክተዋል።

ተቋማት ለተገልጋይ ምቹና ፅዱ እንዲሆኑ ከዋናው መስሪያ ቤት ጨምሮ በ11 ክፍለ ከተሞች ባሉ ለ111 ወረዳዎች ምቹ የሆነ የስራ አካባቢን መፍጠር ስለመቻሉም በመድረኩ ተመላክቷል።

ከኮሪደር ልማት ስራ ጋር ተያይዞ የሰው ሀይልን በማፍራት እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ የተሻለ ውጤት እንዳለ ያነሱት አቶ ጥራቱ በተለይ ለከተማዋ ውበት እና ድምቀት መሰረት የሆኑ ፖሎችን እና መብራቶች በሀገር ውስጥ ከመተካት አንጻር ተጨማሪ ስራን ይጠይቃል ብለዋል።

የአሰራር ስርአትን በማዘመን እና ዘመኑን የሚዋጁ ዲጅታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተገልጋዮች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የተሻለ እንቅስቃሴ መኖሩን ያነሱት ሀላፊው አለም ከደረሰበት ዲጅታል ሲስተም አንፃር አሁንም በርካታ ስራዎችን የሚጠይቅ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

በተለይ በ ኢ ስኩል ዲጅታል ሲስተም ሰልጣኞች በየትኛውም ቦታ ሆነው እንዲመዘገቡ የኮሌጆችን አጠቃላይ መረጃና የክፍለ ጊዜ ድልድል እንዲያገኙ በማድረግ ከ22 ሺ በላይ ሰልጣኞችን መቀበል ስለመቻሉም በውይይቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ባለፍት ስድስት ወራት በአጫጭር ስልጠናዎች ከ93ሺ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉ የተገለፀ ሲሆን ከታቀደው እቅድ አንፃር አሁንም ቀሪ ስራዎችን የሚጠይቅ ስለመሆኑም ተመላክቷል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review