
AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ከ109 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት በተከናወኑ የቅንጅት ስራዎችና በተገኙ ውጤቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያካሄደ ነው።
ቢሮው ባለፉት 6 ወራት ከፌዴራል እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ ከ26 ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት በበጀት አመቱ የ6 ወራት ትግበራ ከታቀደው ገቢ 88 በመቶ በማሳካት 109.81 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ ስለመቻሉ ተነግሯል።

የአሰራር ስርአትን በማዘመን እና የሰው ሀብት ልማትን በማጠናከር የህዝቡን የአገልግሎት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እረገድ ቢሮ በቅንጅት በመስራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ስለመቻሉም ተመላክቷል።
ከተቋማት ጋር በተሰራው የቅንጅት ስራ የገቢ አሰባሰቡ እንዲያድግ ህገ ወጥነት እና የታክስ ማጭበርበር መቆጣጠር እንዲቻል ከማድረግም ባሻገር የተሻለ የአሰራር ስርአተት እንዲዘረጋ ስለማስቻሉም በመድረኩ ተነስቷል።
ከደረሰኝ ግብኝት ጋር ተያይዞ ከተማዋ ማግኘት ያለባትን ገቢ እንዳታገኝ የሚያደርጉ የአሰራር ስርአትን በመቆጣጠር እረገድ ቢሮው መርካቶ ላይ የጀመረው እንቅስቃሴ የተሻለ መሆኑን በማሳሰብ አሁንም ይህንን በመቆጣጠር ረገድ ቅንጅታዊ አስራር የቀጣይ የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባም በመድረኩ ተመላክቷል።
በራሄል አበበ