AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም
ባለፉት ስድስት ዓመታት ብልፅግና ፓርቲ ላከናወናቸው ስኬታማ ተግባራት የህዝቡ አበርክቶ የላቀ እንደነበር የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ገለጹ፡፡
ክፍለ ከተማው “ተቋማዊ ባህል ስርዓታዊ ልህቀት ለዘላቂ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ስድስት ዓመታት የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ከማቅለል ጀምሮ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን ማከናወኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ ፓርቲው ላስመዘገባቸው ውጤታማ ስራዎች የህዝቡ ድርሻ የላቀ ነበር ብለዋል።

በሌማት ትሩፋት እና በከተማ ግብርና የተከናወኑ ስራዎች የመዲናዋን ነዋሪዎች በምግብ ራስን ለማስቻል እና የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ያቀለሉ ተግባራት እንደሆኑም አመላክተዋል፡፡
ያለፉት ስድስት ዓመታት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ በርካታ አይቻሉም የተባሉ ተግባራት የተከናወኑበት ዓመት እንደነበርም አንስተዋል፡፡
በክፍለ ከተማው እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ውይይት በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን እና ውሳኔዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በጽዮን ማሞ