ብልፅግና ፓርቲ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

You are currently viewing ብልፅግና ፓርቲ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

AMN_የካቲት 18/2017 ዓ.ም

ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ባሳለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይ አምባሳደሮች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ፓርቲው በ2ኛ ጉባኤው የዜጎችን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የዛሬው ውይይትም በውሳኔዎች እና አቅጫዎች ላይ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እና ለዓለም አቀፍ ተቋማት የተደራጀ መረጃ ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል።

በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ መግባባት ለመፍጠር ውይይቱ ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሁል፣ የፓርቲው ሁለተኛ ጉባኤ እና ያሳለፋቸው አቅጫዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።

ፓርቲው በሰጠው አመራር በየመስኩ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቅሰው፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ፣የዘርፎች ሪፎርም፣ በምግብ ራስን የመቻል እንዲሁም የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈጻጸምን በአብነት ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ጠንካራ ፓርቲ መገንባት፣ አንድ የሚያደርጉ አሰባሳቢ ትርክቶችን መፍጠር፣ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

በኢኮኖሚ መስክም እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል ከዚህ ዓመት ጀምሮ በቀጣይ ተከታታይ ዓመታት 8 ነጥብ 4 በመቶ አማካይ እድገት ግብ መያዙን መጥቀሳቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review