
AMN- ህዳር 6/2017 ዓ.ም
በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ለብራዚል ፕሬዝዳንት ሊዩዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በብራዚል እና ኢትዮጵያ መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን በመግለጽ በአጋርነት ለመስራትና ግንኙነቱን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዘርፍ፣በተለይም በግብርና የብራዚልን እና የኢትዮጵያን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
አምባሳደር ልዑልሰገድ፣ በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል ያለው የረዥም ጊዜ እና ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ላቀ የስትራቴጂክ አጋርነት ለማሸጋገር የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ለፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በኢትዮጵያ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች እና ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በመሆኑ የብራዚል ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።