ብቁና ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሱ የጤና ባለሙያዎች የማፍራት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል- ዶክተር መቅደስ ዳባ

You are currently viewing ብቁና ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሱ የጤና ባለሙያዎች የማፍራት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል- ዶክተር መቅደስ ዳባ

AMN – መጋቢት 28/2017 ዓ.ም

ብቁ እና ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሱ የጤና ባለሙያዎች የማፍራት ጥረቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 312 የጤና ባለሙያዎች አስመርቋል፡፡

ኮሌጁ ዛሬ ለ12ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው የጤና ባለሙያዎች ውስጥ 117ቱ ሴቶች ናቸው።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ባለፉት ዓመታት የጤና ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በዚህም በሙያቸው የተመሰገኑ እና በህዝብ የተጣለባቸው ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጡ የጤና ባለሙያዎችን በማፍረት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ብቃት ያላቸው እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተላበሱ የጤና ባለሙያዎችን የማፍራት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የዛሬ ተመራቂዎች ለበለጠ ሀገራዊ ኃላፊነት ቃል የገቡበትና የሚዘጋጁበት መሆኑንም አመላክተዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ሲሳይ ስርጉን በበኩላቸው፤ ኮሌጁ የጤና ባለሙያዎችን ሲያስመርቅ ለ12ኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮ ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው ወቅት ያገኙትን እውቀትና ክህሎት መሰረት በማድረግ ማህበረሰባቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review