ተደብቀው የነበሩት ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ተያዙ

You are currently viewing ተደብቀው የነበሩት ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ተያዙ

AMN ታሕሣሥ 27/2017 ዓ.ም

ነዳጅ ጭነው ያለአግባባ በየቦታው ቆመው የሚገኙ የነዳጅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ተይዘው ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አሳወቀ።

የአፋር ክልል ንግድ ቢሮ እና የክልሉ ጸጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ነዳጅ ጭነው በየቦታው ተደብቀው የነበሩ ቦቴዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ መደረጉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ሰርዶ አድማስ በሚባል ቦታ በየጥሻው የተደበቁ ቦቴዎች በፀጥታ አካላት አሰሳ መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሽከርካሪዎቹ እጀባ እንዲሰጥ በማድረግ ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል መባሉን ባለስልጣኑ በመረጃው አመልክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review