ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር እና የቁርዓን ውድድር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል

You are currently viewing ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር እና የቁርዓን ውድድር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል

AMN-መጋቢት 7/2017 ዓ.ም

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ ግብር እና ሀገር አቀፍ የቁርአን የፍጻሜ ውድድር በመስቀል አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የቁርአን ውድድር ማጣሪያ “ቁርአን የእውቀትና የሰላም ምንጭ” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ ቆይቶ፤ ዛሬ በሁለቱም ጾታ ሶስት ሶስት ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜ ደርሰው እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

ፕሮግራሙን ለመታደም በርካታ ህዝበ ሙስሊሞች ወደ መስቀል አደባባይ ተገኝተዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review