የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ የተለያዩ የታሪፍ እርምጃዎችን በመዉሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን በትላንትናው እለት ተጨማሪ የ50 በመቶ ታሪፍ መጣላቸዉ ይታወሳል፡፡
ይህንኑ ጭማሪ ተከትሎ ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ የጣሉትን የ104 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ታሪፉ የዓለማችንን ትልቋን ላኪ ሃገር ቻይናን በእጅጉ የሚጎዳ እና የአሜሪካንን የኢኮኖሚ የበላይነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ ከቻይና ወደ ሀገሯ በሚገቡት ምርቶቸ ላይ የ104 በመቶው ታሪፍ የጣለችው ቤጂንግ ባለፈው ማክሰኞ የ34 በመቶ አጸፋዊ እርምጃ መዉሰዷን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።
በወርቅነህ አቢዮ