ትራምፕ እና ፑቲን በስልክ መከሩ

AMN- ግንቦት 11/2017 ዓ.ም

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ማስቆም በሚቻልበት መፍትሔ ላይ በስልክ መክረዋል።

መሪዎቹ ከስልክ ውይይቱ በኋላ ለጦርነቱ እልባት መስጠት የሚያስችል መፍትሔ ላይ ስለመድረስ አለመድረሳቸው እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ትራምፕ በቀጣይም ጦርነቱን ለማስቆም ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ እንዲሁም ከተወሰኑ የኔቶ ጥምረት አባል ሀገራት መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ከትናንት በስቲያ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተሰኘው የማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በዛሬው ዕለት ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት የስልክ ውይይት “በዩክሬን ያለውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም” ቁርጥ መፍትሄ እንደሚያዋልድ ያላቸውን እምነት ገልጸው ነበር።

ትራምፕ “ዕለቱ ፈጽሞ መጀመር ያልነበረበት አስከፊው ጦርነት የሚያበቃበት ፍሬያማ ቀን እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ማለታቸውንም ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review