ችግሮች በምክክር እንዲፈቱ እና በመነጋገር እንዲስተካከሉ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ፦ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

You are currently viewing ችግሮች በምክክር እንዲፈቱ እና በመነጋገር እንዲስተካከሉ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ፦ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

AMN-መጋቢት 7/2017 ዓ.ም

እንደሀገር የሚፈጠሩ ችግሮች በምክክር እንዲፈቱ እና በመነጋገር እንዲስተካከሉ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ሲሉ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ገለፁ።

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ ቁርአን የትውልድ የህይወት መርህና መመሪያ ነው ብለዋል።

እንደሀገር የሚፈጠሩ ችግሮች በምክክርና በመነጋገር እንዲፈቱ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ አብሮነትን የሚገልፁ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀው፤ የሃይማኖት ተቋማት ህግና ሥርዓት እንዲከበር የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።

በሀገር አቀፉ የቁርአን የፍጻሜ ውድድር ላይ የታደሙት የጠቅላይ ምክር ቤት ኡለማዕ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ሸይኽ ጀይላን ከድር ፣ ቁርአንን ለአላህ ብሎ የተማረና ያስተማረ በሁለቱም ዓለማት ደረጃው ከፍ ያለ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመሃመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review