አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ዘርፈብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት-ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቦ

You are currently viewing አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ዘርፈብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት-ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቦ

AMN – መስከረም 29/2017 ዓ.ም

አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ዘርፈብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቦ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በአልጄሪያ ህዝባዊ ዴሞክራሲዊ ሪፐብሊክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ተቦን አቅርበዋል።

በአልጄሪያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በተካሄደው የሹመት ደበዳቤ የማቅረብ ሥነ ሥርዓት አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ የፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዚደንት ተቦን አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቦ፣ አልጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ዘርፈብዙ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል ።

አምባሳደር ሙክታር በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸው ፣ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ድርጅቱን እንዲጠናከር እና የፖን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ እንዲጎለብት ያደረጉትን ጥረት ማብራራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review