አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ የጣለችውን ታሪፍ ወደ 145 በመቶ አሳደገች

You are currently viewing አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ የጣለችውን ታሪፍ ወደ 145 በመቶ አሳደገች

AMN – ሚያዝያ 3/2017

አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ የጣለችውን ታሪፍ ወደ 145 በመቶ ማሳደጓን ተገለጸ።

በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል የተጀመረው የንግድ ጦርነት በተጋጋለበት በዚህ ወቅት ኋይት ሃውስ በቤንጂንግ ላይ የጣለችውን ታሪፍ 145 በመቶ ማድረሷን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ125 በመቶ ታሪፍ መጣላቸውን ባወጁበት ማግስት ተጨማሪ የ20 በመቶ ታሪክ መጣሉን ከኋይት ሃውስ ይፋ መደረጉን ዘግባው አመላቷል።

ይህም አሜሪካ በሌሎች አገራት ላይ የጣለችውን ታሪክ ለዘጠና ቀናት ያዝ ካደረገች በኋላ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ቻይና ላይ የጣለችውን ታሪፍ ግን ወደ 145 በመቶ ማሳደጓን ነው ቢቢሲ የዘገበው፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review