አሜሪካ እና ሩሲያ በአቡዳቢ የስመ ጥር እስረኞች ልውውጥ ማድረጋቸው ተገለጸ

You are currently viewing አሜሪካ እና ሩሲያ በአቡዳቢ የስመ ጥር እስረኞች ልውውጥ ማድረጋቸው ተገለጸ

AMN – ሚያዝያ 02 /2017 ዓ.ም

አሜሪካ እና ሩሲያ በአቡዳቢ የእስረኞች ልውውጥ ማድረጋቸውን የሩሲያው ፌዴራል ደኅንነት አገልግሎት ይፋ አደረገ።

ሁለቱ ሀገራት እስረኞቻቻውን የተለዋወጡት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ አቡዳቢ ሲሆን ይህም በመካከላቸው ዘላቂ መተማማንን እንደሚፈጥር ተገልጿል።

ልውውጡ በሁለቱ ሀገራት የደህንነት ተቋማት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት አጉልቶ የሚያሳይም ነው ተብሏል።

ከነሐሴ ወር ጀምሮ አሜሪካ እና ሩሲያ እስረኞችን ሲለዋወጡ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥር ወር ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ደግሞ ለሁለተኛው ጊዜ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ የእስረኞች ልውውጥ አሜሪካ አርተር ፔትሮቭ የተባለውን የጀርመን እና የሩሲያ ጥምር ዜግነት ያለውን ነጋዴን ስትፈታ፤ ሩሲያ በበኩሏ ከሰኒአ ካርሊና የተባለቸውን የቀድሞ የባሌ ዳንሰኛ መልቀቋን አልጄዚራ ዘግቧል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review