አምስተኛው የኢትዮ-አልጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
የሁለቱ ሀገራት የጋራ ኮሚሽን የቴክኒክ ስብሰባ ትናንት የተካሄደ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የኮሚሽኑ ስብሰባ በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን ወዳጅነት ከማጠናከር እንዲሁም በበርካታ የትብብር መስኮች ላይ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከመምከር አንጻር ትልቅ አበርክቶ አለው።