አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሲንጋፖር አምባሳደር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሲንጋፖር አምባሳደር ጋር ተወያዩ

AMN-የካቲት 10 /2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ የሲንጋፖር አምባሳደር ሲቭራጃን በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ ከሲንጋፖር ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በፖለቲካ እና ኢኮኖሚ መስኮች በተለይ በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሲቭራጃ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የበርካታ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ አዲስ አበባ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች የሚካሄድባት መሆኗን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በቅርቡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሲንጋፖር ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ከአምባሳደሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ሁለቱ አገራት በባለብዙወገን የግንኙነት መድረክ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review