አርሶ አደሩ ምርቱን ማስያዣ አድርጎ የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ፕሮጀክት ወደ ሥራ ገባ

You are currently viewing አርሶ አደሩ ምርቱን ማስያዣ አድርጎ የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ፕሮጀክት ወደ ሥራ ገባ

AMN – ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም

አርሶ አደሩ ምርቱን ማስያዣ አድርጎ የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ፕሮጀክት ወደ ሥራ መግባቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከኤጂ አር ኤ፣ ከአይ ኤፍ ሲ እንዲሁም ዘርፉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የመጋዘን ደረሰኝ አገልግሎት ስርዓትን የሚያጠናክር ፕሮጀክት ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የግብርና ምርቶችን ግብይት የሚያሳልጥ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት መሆኑን በሚኒስቴሩ የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ ተናግረዋል፡፡

ሥርዓቱ የምርት ብክነትን ለመከላከል፣ ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የወጪ ንግድን ለማሳለጥ እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በማቅረብ የአርሶ አደሩንና በግብርና እሴት ሰንሰለት ላይ የተሰማሩ የዘርፉ ተዋንያንን ውጤታማነትና አቅም የሚያሳድግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የመጋዘን ደረሰኝ አገልግሎት ስርዓቱ አርሶ አደሩ ምርቱን ማስያዣ አድርጎ የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ይህ አገልግሎት አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በተሻለ ዋጋ ለገበያ እንዲያቀርብ የሚያስችል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ ዘመናዊ የመጋዘን ደረሰኝ አገልግሎት ስርዓትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review