AMN – መጋቢት 12/2017
በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ የሚገኘው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል ።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፈዋል።
በምድብ አንድ የተሳተፈችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ4:11.87 አንደኛ ደረጃ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፍ ችላለች፡፡

በምድብ ሶስት የተሳተፈችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ4:12.25 አንደኛ ደረጃ በመውጣት ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ምድብ ሁለት ላይ የተወዳደረች ሲሆን በ4:10:61 ሰዓት 4ኛ ደረጃ በመያዝ ስታጠናቅቅ ፣ለፍፃሜ ለማለፍ ያደረገችው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡