አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመመረቅ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ገለጹ

You are currently viewing አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመመረቅ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ገለጹ

AMN – ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ ወደ ተሟላ ሥራ የገቡ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመመረቅ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጎንደር ገብተዋል፡፡

የሦስተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል የሆነውን ክልላዊ ኤክስፖ እንደሚከፍቱና እና በንቅናቄው ወደ ተሟላ ሥራ የገቡ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በጎንደር እንደሚከፍቱ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የቤተ እምነትና የኅብረ ብሔራዊነት ማዕከል፣ ከኢትዮጵያ ቀደምት የሥልጣኔና የጥበብ ምልክቶች አንዷ የሆነችውና በታሪካዊ የልዕልና ጉዞ ላይ የምትገኘው ጎንደር ገብተናል ብለዋል፡፡

በጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ የሞቀ አቀባበል ላደረጉልን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ የጎንደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ አመራሮችና እና የጎንደር ከተማ ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በቆይታችንም የሦስተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል የሆነውን ክልላዊ ኤክስፖ የምንከፍት፣ በንቅናቄው ወደ ተሟላ ሥራ የገቡ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የምንመርቅ፣ በከተማዋ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንም የምንጎበኝ ይሆናል ብለዋል አቶ ተመስገን በመልክታቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review