AMN – የካቲት 15/2017 ዓ.ም
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የቱርኩ አክ ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቱርክ አንካራ ገብተዋል።
አቶ አደም፣ አንካራ ሲደርሱ የአክ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና በቱርክ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሀመድን ጨምሮ የኤምባሲው አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከብልፅግና ፓርቲ ማኀበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የቱርኩ አክ ፓርቲ ከፊታችን ፌብሩዋሪ 23 ጀምሮ ጠቅላላ ጉባዔውን እንደሚያካሂድም ተመላክቷል፡፡