አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ለቆዩትና በጥንቃቄ ለሰጡት አመራር አመሰግናለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ለቆዩትና በጥንቃቄ ለሰጡት አመራር አመሰግናለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – መጋቢት 29/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ በትግርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልእክት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ለቆዩትና በጥንቃቄ ለሰጡት አመራር አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

በኢፌድሪ ሕገ መንግስት 62 (9)፣ በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 15 (3) እና ደንብ ቁጥር 533/2015 እንዲሁም በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት መሠረት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ሆነው ላበረከቱት፥ በተለይ የተገኘውን ሰላም ወደ ኃላ እንዳይመለስ የነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ እና አመራር የፌዴራል መንግስት እውቅና እንዳለውና፣ በቀጣይ ስራዎችም ተቀራርበን እንደምንሠራ እያረጋገጥኩ፤ ለነበርዎት ቆይታ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review