አዲስ አበባ 11ኛውን የአይ. ዲ4 አፍሪካ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመጪው ግንቦት ወር ታስተናግዳለች

You are currently viewing አዲስ አበባ 11ኛውን የአይ. ዲ4 አፍሪካ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመጪው ግንቦት ወር ታስተናግዳለች

AMN – የካቲት 20/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ በዲጂታል ማንነት ማለትም በመታወቂያ እና በሲቪል ምዝገባ ላይ ያተኮረውን የ2025 11ኛውን የአይ. ዲ4 አፍሪካን ዓለም አቀፍ ጉባኤ የፊታችን ግንቦት ወር እንደምታስተናግድ ተገለጸ፡፡

የ2024 የአይ ዲ4 አፍሪካ 10ኛው ጉባኤ በኬፕታዎን ፣ ደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በተከናወነበት ወቅት ለ2025 አዘጋጅነት ተፎካካሪ ሃገራትን በማሸነፍ ኢትዮጵያ አስተናጋጅ እንድትሆን መመርጧ ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት አዲስ አበባ ጉባኤውን በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስተባባሪነት በግንቦት ወር እንደምታስተናግድ ተመላክቷል፡፡

በጉባኤው ላይ የተለያዩ ሃገራት ሚኒስትሮች፣ የሲቪል ምዝገባ እና የመታወቂያ ዘርፍ የስራ ሃላፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ አህጉር አቀፍ እና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ጨምሮ ከ2ሺ በላይ ተሳታፊዎች ይታደሙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review