አዲስ አበባ ከተማን በከተማ ግብርና ዘርፍ ከአፍሪካ ከተሞች ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ ተናግረዋል ።
መንግስት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋትን ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በዜጎች ህይወት እና የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ረገድ ለውጥ መመዝገቡን ኮምሸነሩ ገልፀዋል ።
በተለይም ጥራት ያለውና በቂ ምርት ለማቅረብ በእርባታ ዘርፉ የመኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ኮሚሽኑ በማህበራት የተደራጁ ከመኖ አምራቾች ጋር በመነጋገር በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል ።
ኮሚሽኑ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ከሚሆኑ አርሶአደሮችና አርብቶ አደሮች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
በአይናለም አባይነህ እና በአለሙ ኢላላ