“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ስንል የነዋሪዎቿን ህይወት እና አኗኗር ማሳመርንም የሚያካትት ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ኅዳር 30/2017 ዓ.ም

“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ስንል የነዋሪዎቿን ህይወት እና አኗኗር ማሳመርንም የሚያካትት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ለዚህ አንዱ ማሳያ የሆነው ለካሳንችስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የገነባነዉ ማዕከል ነዉ ሲሉ ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዛሬ አገልግሎት የሚጀምረው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ:-

• በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ መኖሪያ መንደር ነው።

• 1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአስፋልት መንገድ አለው።

• ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል አለው።

• በ2 ወር ጊዜ ዉስጥ የተገነቡ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ ይዟል።

• በ3 ሺፍት ለ270 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገርያ ፋብሪካ አለው።

• 500 አረጋዉያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል አለው።

• በቀን 60 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የዕህል ወፍጮዎችን ይዟል።

• ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ አለው።

• ⁠ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችና መናፈሻዎች ተገንብተዋል።

• በቋሚ እና በጊዜያዊነት ለ1646 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review