አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን – አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን – አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN – ሚያዚያ 07/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ2017 በጀት አመት የ9 ወራት የፓለቲካና የድርጅት ስራዎችን ግምገማ “ትጋት ምልዐት በቃሊቲ” በሚል መሪ ሀሳብ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

ባለፉት 9 ወራት ግዙፍ እቅዶችን አቅደን የተሳካ ውጤት አሳክተናል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ሙሉ እይታና ትግበራ ይፈልጋል ብለዋል።

አዲስ አበባን ከቆሻሻ የፀዳችና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስሟን የሚመጥን ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ሁሉም ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ ያለ አካል በትጋት በመስራት እንደሚገባውም አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡

የ9 ወራት ትግበራ በታቀደው ልክ መሰራቱን የገለጹት አቶ ሞገስ፣ ቀረ እቅዶችን ለመፈፀም ሁሉም በትጋት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review