አገልግሎቶችን ማዘመንና ምቹ ማድረግ ዘላቂ ኢኮኖሚን ለመገንባት ያስችላል ፡- የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

You are currently viewing አገልግሎቶችን ማዘመንና ምቹ ማድረግ ዘላቂ ኢኮኖሚን ለመገንባት ያስችላል ፡- የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

AMN – ታኅሣሥ 20/2017 ዓ.ም

የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማዘመንና ምቹ ማድረግ ዘላቂ ኢኮኖሚን በአገራችን ለመገንባት የሚያስችል ትልቅ ኢንቨስትመንት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት “ስነምግባራዊ አገልጋይና አመራር ለሁለንተናዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ሃሳብ በየደረጃው ላሉ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

አዲስአበባን እንደ ስሟ ለማስዋብና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በርካታ የልማት ስራዎችን ስለማከናወኑ በመድረኩ ተመላክቷል።

ከመዲናዋ የልማት ስራዎች እኩል ለህብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማዘመንና ቀልጣፍ ማድረግ ካልተቻለ ለውጡ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ይህንን ተመጋጋቢ ለማድረግ በተቋም ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በትኩረት መስራት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል

የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማዘመንና ምቹ ማድረግ ዘላቂ ኢኮኖሚን በአገራችን ለመገንባት የሚያስችል ትልቅ ኢንቨስትመንት መሆኑም ተገልጿል።

በመልካም አመለካከት ቀልጣፍና ውጤታማ አገልግሎት ለዜጎች በመስጠት የተቋማትን ቅቡልነት ማሳደግ እንደሚገባ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን የሚተገበሩ ሁሉም አሰራሮች ለተገልጋዩ ግልፅ መሆን እንደሚገባቸውም ተመላክቷል።

አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ቀልጣፍ ለማድረግ ምቹ ከባቢን መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን በስልጠናው የተገለፀ ሲሆን ለዚህም ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ማስገባት ያስፈልጋል ተብሏል።

በስልጠናውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣እንዲሁም የክፍለከተማው ስራ አስፈፃሚ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review