አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ድምጽና ተሰሚነት ሊጠናከር ይገባል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ድምጽና ተሰሚነት ሊጠናከር ይገባል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – የካቲት 8/2017 ዓ.ም

አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ድምጽና ተሰሚነት ሊጠናከር ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በመልዕክታቸውም፤ በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም ፍትህ እና ብልጽግና ለማረጋገጥ ቅኝ ግዢዎች ባስቀመጡት የሀገራት ድንበር ምክንያት ከሚፈጠር የጂኦ-ፖለቲካ ውጥረት መውጣት አለብን ብለዋል።

አህጉሪቷ ያላት ብዝሃ ማንነትም አካታች መንግስት ለመመስረት ምቹ እድል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በማበጀት ዘላቂ ሰላምን በጋራ ማረጋገጥ አለብን ሲሉም ነው የተናገሩት።

አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ድምጽና ተሰሚነት ሊጠናከር ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ደግሞ ነባሩ የዓለም ስርዓት ሊሻሻል ይገባል ብለዋል።

በሌላ በኩል አፍሪካ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ውድድር ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆን እንዳለባት ተናግረዋል።

በተለይ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የፋይናንስ እና ሞባይል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ አፍሪካዊያን በትብብር መስራት እንደሚጠበቅባቸው አውስተዋል።

አፍሪካ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ አማራጮች እንደሚያስፈልጋትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።

በአሰግድ ኪዳነማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review