ኢራን እና አሜሪካ በኒኩለር ዙሪያ በኦማን ንግግር ሊያካሄዱ ነው

You are currently viewing ኢራን እና አሜሪካ በኒኩለር ዙሪያ በኦማን ንግግር ሊያካሄዱ ነው

AMN – ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው የእጅ አዙር የኒኩለር ንግግር የኦማን ዋና ከተማ ሙስካት እንደሚካሄድ ኢራን አስታወቀች።

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን ወደ ድርድሩ የማትመጣ ከሆነ ከፊቷ ከባድ አደጋ ይጠብቃታል” በማለት ዝተዋል።

ኢራን በበኩሏ “እኛ የምንፈልገው የኒውክለር መሳሪያ ሳይሆን ማዕቀብ እንዲነሳልን ነው” ማለቷ ይታወሳል።

ኢራን የኒውክለርን ጉዳይ ቅድሚያ የምትሰጠው ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን እና ይህም በቀጣይ ለሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች መተማመንን የሚፈጥር መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አጽንዖት የሰጡት ጉዳይ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review