ኢራን የኒውክሌር አቋሟን ልትቀይር እንደምትችል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለፁ

You are currently viewing ኢራን የኒውክሌር አቋሟን ልትቀይር እንደምትችል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለፁ

AMN-ሰኔ 12/2017

አሜሪካ የእስራኤል- ኢራን ጦርነትን ካስቆመች የኒውክሌር ሃገራቸው አቋሟን ልትቀይር እንደምትችል የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ፍንጭ ሰጡ።

ኢራን ከአሜሪካ ጋር የስልክ ንግግር አድርጋለች።

የእስራኤል – ኢራን ግጭት ተፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት ላይ የመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ስቲቭ ዊትሆቭ እና የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ የስልክ ንግግር ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ሁለቱ የስራ ኃላፊዎች ባሳለፍነው ሳምንት በኢራንና እስራኤል መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የስልክ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የስልክ ልውውጡ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመሻት ያለመ ነው ተብሏል።

ለስልክ ንግግሩ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማቶች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከሆነ እስራኤል በኢራን ላይ የከፈተችውን ጦርነት አሜሪካ ካስቆመች ኢራን የኒውክሌር መርሀግብሯ ላይ ያላትን አቋም ልትቀይር ትችላለች ሲሉ አራቅቺ ለዊትሆቭ ፍንጭ ሰጥተዋል ።

“ኢራን ወዳቋረጠችው የኒውክሌር ንግግር ልትመለስ ትችላለች ፤ ነገር ግን እስራኤል ጥቃት ማድረሷን ከቀጠለችበት ይህ ሊሆን አይችልም” ነው ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና የአውሮፓ ህብረት አርብ እለት ከአራቅቺ ጋር ተገናኝተው ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸውንም የሮይተር ዘገባ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review