AMN-የካቲት 19/2017 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም ለተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት ደንበኞች የሚሆን ሰባት አዳዲስ የዲጅታል አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አሰፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ለአገልግሎት ይፋ የተደረጉ ቴክኖሎጂዎች ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያቀላጥፍና አገልግሎቶችን በብቃት ለመስጠትና ለፋይናንስ ዘርፉ መፍትሄ ይዞ የመጣ ነው ብለዋል።
ይፋ ከተደረጉት አዳዲስ አገልግሎቶች መካከልም የአርሶአደር፣የትምህርት ፣የፋይናንስ ተቋማትን እንዲሁም የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተደራሽነትና ዲጅታል አገልግሎቶችን በቀላሉ የሚያቀላጥፍ ቴክኖሎጂዎች ይገኙበታል ብለዋል።
በዓለሙ ኢላላ