ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የ5ኛው ትውልድ ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀመረ

You are currently viewing ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የ5ኛው ትውልድ ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀመረ

AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የ5ጂ (5ኛው ትውልድ) ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀምሯል።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ አገልግሎቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

የ130 አመት እድሜ ባለጸጋ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም እራሱን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እያስታጠቀ ያለ ሀገራዊ ተቋም መሆኑም በመርሐ ግብሩ ተገልጿል።

ተቋሙ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን እያደረግ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ባለፉት አመታት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን እና ይህም የሀገራችንን ልማት ለማፋጠን በሚያስችል መልኩ እየተከናወነ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።

ከ80 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ያፈራው ተቋሙ በአፍሪካ ከሚገኙ ኦፕሬተሮች አንደኛ፣ ከአለም ደግሞ 16ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ተደራሽ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የተገኙ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ዛሬ በይፋ የተጀመረው የ5ኛው ትውልድ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅማ ከተማ ተደራሽ መሆኑም ተመላክቷል።

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review