ኢትዮጵያ ለባለብዙወገን ግንኙነት እና በጋራ ደኀንነት ላይ መሠረት ላደረገው የተመድ ሥርዓት ያላትን የረዥም ጊዜ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች-አቶ ማሞ ምህረቱ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለባለብዙወገን ግንኙነት እና በጋራ ደኀንነት ላይ መሠረት ላደረገው የተመድ ሥርዓት ያላትን የረዥም ጊዜ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች-አቶ ማሞ ምህረቱ

AMN – የካቲት 18/2017 ዓ.ም

በብሔራዊ ባንክ ገዥ እና የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉዳይ ዋና አስተባባሪ አቶ ማሞ ምህረቱ የተመራው እና ምክትል አስተባባሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተካተቱበት ልዑካን ቡድን በብራዚል መዲና እየተካሄደ ባለው የብሪክስ አባል አገራት የዋና አስተባባሪዎች እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው።

ዋና አስተባባሪው(ሼርፓ) አቶ ማሞ ምህረቱ በስብሰባው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለባለብዙወገን ግንኙነት እና ለጋራ ደኀንነት ላይ መሠረት ላደረገው የተመድ ሥርዓት ያላትን የረዥም ጊዜ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

ዋና አስተባባሪው በብራዚል የብሪክስ ፕሬዝዳንትነት ዓመት ከኢትዮጵያ ግቦች መካከል አንዱ የአዲሱ የብሪክስ የልማት ባንክ አባል መሆን እንደሆነ ገልጸዋል።

የብራዚል የብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ዓመት ስድስት ቁልፍ ትኩረቶችን ያስቀመጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

የዓለም ጤና ስርዓት፣የዓለም አቀፍ ስርዓትን የማሻሻል ጥረት፣ለአየር ንብረት ለውጥ የፋይናንስ ግኝት፣ሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደር፣ የደቡብ ደቡብ ትብብር እና የብሪክስ ተቋማዊ ልማት ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review