ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይዘውት የመጡትን መልእክት ተቀብያለሁ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል ያሉ ሲሆን፣ በደቡብ ሱዳን ወቅታዊውን የጸጥታና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት፣ ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥቻለሁ በማለት ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።