ኢትዮጵያ ቀጣናዊና አህጉራዊ ትስስሮችን በማጠናከር ረገድ የዳበረ የመሪነት ሚና አላት

You are currently viewing ኢትዮጵያ ቀጣናዊና አህጉራዊ ትስስሮችን በማጠናከር ረገድ የዳበረ የመሪነት ሚና አላት

AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቀጣናዊና አህጉራዊ ትስስሮችን በማጠናከር ረገድ የዳበረ ቁርጠኝነትና የመሪነት ሚና ያላት ሃገር ናት ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ በአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በጋራ በተዘጋጀው ከቪዛ-ነጻ እንቅስቃሴ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን ርዕሰ ጉዳይ የሚኒስትሮች ስትራቴጂካዊ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ ትስስር ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በመድረኩ ላይ እንዳጋሩም ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ቀጣናዊና አህጉራዊ ትስስሮችና ከማጠናከር ረገድ የዳበረ ቁርጠኝነትና የመሪነት ሚና ያላት ሃገር ናት ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊያን የነፃነት ቀዲድል የሆነች፣ በራስ ለመተማመን ስነልቦና መሰረት የጣሉ ድሎችን ያስመዘገበች፣ ከአፍሪካውያን አልፋ ለመላው ጥቁር ህዝቦች የይቻላል መንፈስን ያሰረጸች ሃገር ናት ሲሉም ገልጸዋል።

ከለውጥ ወዲህ በተገበርነው የሃገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ገበያችንን ለመላው አፍሪካዊያን ክፍት አድርገናል ያሉት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከጫፍ ጫፍ እያስተሳሰረ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለቱሪዝምና ለቢዝነስ ተመራጭ መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ገልጸው ንግድና ኢኮኖሚ ትስስርን ከማጠናከር አንጻር የመሪነት ሚናችንን መወጣታችንን እንቀጥላለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review