ኢትዮጵያ ቃል የገባችባቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነቶች በሙሉ ቆጥራ የምታስረክብ ሀገር ናት- የተመድ የልማት ፕሮግራም

AMN-ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ቃል የገባችባቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነቶች በሙሉ ቆጥራ የምታስረክብ ሀገር መሆኗን የተባበሩት መንግስታት ድርጂት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ገለጸ፡፡

ያለፈውን አንድ ዓመት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ የሰራቻቸው ስራዎች ዙርያ በኢትዮጵያ ፓቪሊዮን ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያ ከፖሊሲ ለውጥ ጀምሮ በአረንጓዴ አሻራ በታዳሽ ሀይል እንዲሁም በምግብ ሰብል እራስን ለመቻል በርካታ ስራዎችን እየሰራች መሆኑን እና በCOP28 የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነቶችንም መፈፀሟን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፉ ተናግረዋል፡፡

የልማት አጋር ድርጅቶቹ ዓለም የተራቆቱ አካባቢዎችን በደን ለመሸፈን የሀይል አማራጮችን ሙሉ በሙሉ በታዳሽ ሀይል ለመተካት የያዘውን እቅድ ኢትዮጵያ ቀድማ የጀመረች ሀገር ናት ብለዋል፡፡

በተለይም በአረንጓዴ አሻራ እየተሰራ ያለው ስራ ለተቀረው አለም ምሳሌ መሆን የሚችል መሆኑን መናገራቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ እየሰራች ላለችው ስራ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል።

All reactions:

3535

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review