ኢትዮጵያ በ3ኛው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚያዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ በ3ኛው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚያዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

AMN – ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

በኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሐሰን ሞዓሊን የተመራ የልዑካን ቡድን በቴህራን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚያዊ ጉባኤ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ኮንፍረንሱ በዋናነት በኢራን እና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የኢንዱስትሪ፣ የንግድና የኢቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር አተኩሮ የሚካሄድ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዝሽኪያን በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢራን በጤና፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ እና በግብርና ያስመዘገበችውን ስኬት በሚመለከት ልምድ፣ ተሞክሮና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ አገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

በኢራንና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን በመጪው ዓመት ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱም በኮንፈረንሱ ላይ መጠቆሙን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review