ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል እየሰራች ነው- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

You are currently viewing ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል እየሰራች ነው- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም

አፍሪካ በዓለም ደረጃ የምትታወቅበትን የዕርዳታ ጥገኝነት ታሪክ ለመቀልበስ እና በምግብ ራስን ለመቻል ኢትዮጵያ ብርቱ ጥረት እያደረገች መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን የሚያሳድግ ፖሊሲ በመተግበር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ በዘላቂነት ራስን ለመቻል እየሰራች መሆኗንም ነው መግለጫው ያስገነዘበው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ሥድስት ዓመታት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ፖሊሲዎችን ወደተግባር በመቀየሩ የምግብ ዋስትናን ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት በምግብ ራስን ለመቻል ዓላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ኢትዮጵያን ከእርዳታ ጥገኝነት በማላቀቅ ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን መግለጫው አመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review