ኢትዮጵያ እና ሀንጋሪ በኢኮኖሚ መስክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

AMN- ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሀንጋሪ አምባሳደር አምባሳደር አቲላ ቶማስ ካፕኒይ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

ሁለቱ አካላት የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ሀንጋሪ በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል በመስጠት ያበረከተችውን አስተዋፅኦ አድንቀዋል።

በቀጣይም የሁለቱ አገራት ግንኙነት በኢኮኖሚ መስክ የበለጠ መጠናከር እንዳለበት ገልጸው:የሀንጋሪ ኩባንያዎች በማምረቻ፣ በግብርና እና ማዕድን ዘርፍ በኢትዮጵያ እንዲሠማሩ ጠይቀዋል።

አምባሳደር አቲላ ቶማስ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ሀንጋሪ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ኢንቨስትመንት፣በአቅም ግንባታ እና በሰብአዊ ድጋፍ ያላትን ግንኙነት የበለጠ አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review