የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ከሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሞሮኮ የሦስት ቀናት የስራ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ።
ሚንስትሯ በጉብኝታቸው ወቅት ከሞሮኮ መንግስት ብሔራዊ መከላከያ አስተዳደር ተወካይ ሚኒስትር ከሆኑት አብደላቲፍ ሉዲ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅት ሁለቱ አገራት የመከላከያ እና ደህንነት ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ኢንጅነር አይሻ በሞሮኮ በሚኖራቸው ቆይታ የሞሮኮ የመከላከያ መሰረተ ልማቶችን ጉብኝት ያካሂዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።